አምስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ላይ ያቀረበው ሪፖርት መሰረተ ቢስ መሆኑን ተገለጸ

አዲስ አበባ ግንቦት 2/2000/ዋኢማ/ አምስቲ ኢንተርናሽናል ሶማሊያ በሚገኘው የኢትዮጵያን ጦር በተመለከተ በቅርቡ ያቀረበው ሪፖርት ተቀባይነት የሌለውና መሰረተ ቢስ መሆኑን በደቡብ አፍሪካ የሶማሊያ አምባሳደር አስታወቁ።

አምባሳደር አብዱልከሪም ፋራህ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያና የሶማሊያ የሽግግር መንግስት ጦር በሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት ውጤታማ ስራ በመስራት ላይ ናቸው።

ምባሳደር አብዱልከሪም ፋራህ

በአልቃይዳ የሚደገፉት እንደ አል-ሸባብ የመሳሰሉ የአሸባሪ ቡድኖች በሶማሊያ ሰላማዊ ሰዎችን በማጥቃትና የሀገሪቱን ሰላምና መረጋጋት በማሳጣታቸው ለፍርድ መቅረብ ይገባቸዋል ብለዋል።

አምስቲ ኢንተርናሽናል አሽባሪዎች በኢትዮጵያ ጦር ላይ የሚያካሂደውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳን በመቀበል ያቀረበው ሪፖርት መሰረተ ቢስና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አምባሳደር አብዱልከሪም ፋራሂ አስታውቀዋለ።

ድርጅቱ ያወጣው ሪፖርት ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት በመስራት ላይ ያሉትን አገራት ተነሳሳሽነት የሚጎዳ እና በመደረግ ላይ ላለው የሰላም ጥረት ላይ ጥቁር ነጥብ በመጣል ለአሸባሪዎች ያዳላ መሆኑን አምሳደሩ ተናግረዋል።

እንደአምባሳደሩ ገለጻ፤ በአሁኑ ጊዜ በሶማሊያ እየተኘዘገበ ያለው ፖለቲካዊ ለውጥ አዎንታዊ በመሆናቸው የፀጥታው ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ ነው ብለዋል ።

በሀገሪቱ አሸባሪዎች አልፎ አልፎ በሚፈጽሙት ጥቃት የሚከሰቱት የፀጥታ መጓደሎች በኢትዮጵያ፣ በሶማሊያ የሽግግር መንግስት፣ በአፍሪካ ሕብረትና በሌሎች ሰላም ወዳድ አካላት ለመቀነስና ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን አምባሳደሩ አስረድተዋል።

በአገሪቱ የተፈጠረውን ሰብአዊ ቀውስ ለመፍታት ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ያደረገው ሰብኣዊ ዕርዳታ ከችግሩ ስፋት አንጻር በጣም አነስተኛ ነው ያሉት አምባሳደሩ፤ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በሶማሊያ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀለውን ማህበረሰብ የሰብአዊ ዕርዳታ እንዲያቀርብ ጥሪ ማስተላለፉቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል።