መልካም አስተዳደርን የማስፈን ግባችንን በጋራራ ጥረት ተግባራራዊ በማድረግ ልማታችንን እናፋጥናለን

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የመንግሥትን አቋም የሚተነትን ጽሑፍ

ማስታወቂያ ሚኒስቴር

ግንቦት 1 ቀን 2000 ዓ.. 

የኢትዮጵያ መንግሥት ልማትን ለማፋጠንና የአገራራችንን ህዝቦች ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ብልጽግና እውን ለማድረግ የተለያዩ ፖሊሲዎችንና ስትራራቴጂዎችን ነድፎ ተግባራራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በተለይም አገሪቱን ከኋላቀርነትና ከድህነት ለማላቀቅ በሚያስችል አቅጣጫ ፖሊሲዎችን ተግባራራዊ ማድረግ በመጀመሩ ካለፉት አምስት ዓመታት ጀምሮ የዕቅድ አፈፃፀማችን ውጤታማ እየሆነ እንደመጣ ተረጋግጧል፡፡ ለዚህም አንዱ ማሳያ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በአገር ደረጃ እየተመዘገበ መምጣቱ ነው፡፡

እየተገኘ ያለውን አበረታች የኢኮኖሚ ዕድገት ቀጣይነት ለማረጋገጥም መንግሥት በየጊዜው ተጨማሪና አዳዲስ የፖሊሲ አፈፃፀም ስልቶችን በመንደፍ ሥራራ ላይ እንዲውሉ እያደረገ ይገኛል፡፡ በአጭር ጊዜ ዕቅድ የሚሌኒየሙን የልማት ግቦች በአገር ደረጃ ከማሳካትና ብሎም ዘላቂ ልማትን በቀጣይነት ከማረጋገጥ አኳያ እስካሁን የተከናወነው ተግባር አበረታችና ተስፋ ሰጭ ሲሆን፣በቀጣይም ይህን ጥረት ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ ይሆናል፡፡ በዚህ ረገድም የህብረተሰቡን፣ የመንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ተነሳሽነት በማጐልበት ሁሉም ወገኖች ለልማት፣ ለሰላም፣ ለዴሞክራራሲያዊ ስርዓት ግንባታና ለመልካም አስተዳደር መስፈን የበኩላቸውን እንዲወጡ ማስቻል ተገቢ ይሆናል፡፡

ለፖሊሲዎችና ስትራራቴጂዎች ተፈፃሚነትና ውጤታማነት መልካም አስተዳደርን በሁሉም ደረጃና የአስተዳደር እርከኖች ማስፈን መንግሥት ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር ነው፡፡ ዜጐች ሰብአዊና ዴሞክራራሲያዊ መብቶቻቸውን በአግባቡ ተጠቅመው አገራራቸውን በባለቤትነትና በኃላፊነት ስሜት ለማልማት መልካም አስተዳደርን ማስፈን የግድ ይላል፡፡ በየደረጃው በተዋቀሩ መንግሥታዊ አካላትና የአስተዳደር ዕርከኖች ውስጥ የመልካም አስተዳደር መኖር ልማትን ለማፋጠንና የዜጐች ፍትሀዊ የአገር ሀብት ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ከመሆኑ በተጨማሪ ለሰላማዊና ዴሞክራራሲያዊ አስተዳደር መጐልበት መሠረት ነው፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የአገሪቱ ህገመንግሥት በግልጽ ባስቀመጣቸው ድንጋጌዎች መሠረት ዜጐች የሰብአዊና ዴሞክራራሲያዊ መብቶች እኩል ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ የሚያስችሉ እርምጃዎችን በመውሰድ Kተግባራራዊ’†¨< ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ አንጻርም ከሙስና ጋር ተያይዞ ስር ሰዶ የኖረውን የመልካም አስተዳደር ዕጦት ለማስወገድ መንግሥት የተለያዩ እርምጃዎችን ሲወስድ ቆይቷል፡፡ በቀጣይም ይህ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ መንግሥት ይህን የአገር ዕድገትና የህብረተሰብ ጠንቅ የሆነውን ማኀበራራዊ ችግር ከመሰረቱ ለመፍታት በሚያግዝ መልኩ የተለያዩ ህጋዊ ማዕቀፎችንና አሰራራሮችን የዘረጋ ከመሆኑ በተጨማሪ ተቋማዊ አደረጃጀት ያላቸው አስፈፃሚ አካላትን አቋቁሟል፡፡

በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት አስፈፃሚ አካላትና የአስተዳደር እርከኖች እንዲሁም የፍትህ አካላት ህብረተሰቡ የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ በሚሆንበትና ህገ መንግሥታዊ የዜጐች መብቶች ተግባራራዊ በሚሆኑበት መልኩ በኃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ ህገ መንግሥቱ በሚፈቅደውና ከዚህ በሚመነጩ ህጐችና የአፈፃፀም መመሪያዎች ላይ በመመስረት የዜጐችን ሰብአዊና ዴሞክራራሲያዊ መብቶች ለማረጋገጥ መንግሥት የህዝብ እንባ ጠባቂ፣ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንንና የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽንን አቋቁሟል፡፡ ተቋማቱን ይበልጥ በማደራራጀትና በማጠናከር የህብረተሰቡን መሉ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ ደረጃ እንዲገኙ የማብቃት ሥራራ በመንግሥት በኩል በቀጣይ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር ነው፡፡

ተቋማትን ማቋቋምና ማደራራጀት የራራሱ ፋይዳ ያለው ቢሆንም በራራሱ ብቻ ግን የመጨረሻ ግብ አይሆንም፡፡ በመሆኑም የዜጐችን ሰብአዊና ዴሞክራራሲያዊ መብቶች ከማስከበርና መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አኳያ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት አካላትና መላው ህብረተሰብ በጋራራ ሊንቀሳቀሱ ይገባል፡፡ በዚህ ረገድ የዜጐችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በመንግሥት የወጡ ፖሊሲዎችን፣ የአፈፃፀም ስልቶችንና እነዚህን ለማስፈፀም የተደራራጁ ተቋማትን ህብረተሰቡ ሰብአዊና ዴሞክራራሲያዊ መብቶቹን ተጠቅሞ የበኩሉን የዜግነት ድርሻ በመወጣት ይበልጥ ሊያጠናክራራቸው ይገባል፡፡

ሙስና እና ብልሹ አስተዳደር የልማታችን ዋነኛ ማነቆ እንደሆነ ተገንዝበን ልናወግዘውና ልንታገለው ይገባል፡፡ የሲቪል ሰርቪሱ መቋቋም ከምንም በላይ ለሕዝቦች መብትና ጥቅም መከበር ብሎም ለአገር ዕድገት እንደመሆኑ በሕዝብ አገልጋይነት ስሜት መንቀሳቀስ ይጠበቅበታል፡፡ ህብረተሰቡም ለአድሎአዊና ሙስና ተግባር ተባባሪ ሳይሆን ህገ መንግሥታዊና የዜግነት መብቱን ተጠቅሞ የጋራራና አገራራዊ ጥቅሞቹን ለማስከበር ትኩረት ሰጥቶ መስራራት ይኖርበታል፡፡ መንግሥትም የዚህ ዓይነቱን የህብረተሰቡን ጥረት ደግፎ የሚቆም ሲሆን ህገ ወጥና የዜጐችን መብት የሚፃረሩ ተግባራራትን በህብረተሰቡ ሙሉ ተሳትፎ በመከታተል ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፡፡

ስለሆነም ፀረ ልማትና አደናቃፊ ሁኔታዎችን ተቋቁመን ሀገራራችን የተያያዘችውን የልማት፣ የሰላም፣ የዴሞክራራሲያዊ ስርዓት ግንባታና መልካም አስተዳደርን የማስፈን ጥረቶች አጠናክረን በመቀጠል አገራራችንን ከድህነትና ኋላ ቀርነት ማውጣት ይኖርብናል፡፡ የመልካም አስተዳደር ስርዓት መስፈን ለአገራራችን ልማት ያለውን ቁልፍ ሚና ተገንዝበን ሁላችንም በአገራራዊ የዜግነት ስሜት በጋራራ እንንቀሳቀስ፡፡

Back