ኢትዮጵያ የልማት ግቧን ለማሳካት ርብርብ እያደረገች እንደምትገኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ

  • PDF

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2004 (ዋልታ) - ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ስትራቴጂዋን በማስረፅ የልማት ግቧን ለማሳካት ርብርብ እያደረገች እንደምትገኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ተናገሩ።

አቶ ሃይለማሪያም ዛሬ የመስሪያ ቤታቸውን የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል።

በዚሁ ወቅት እንዳሉት ሀገሪቱ የኢንቨስትመንትና የንግድ ማዕከል እየሆነች መጥታለች።

ባለፉት ስድስት ወራት 186 የውጭ ባለሃብቶች ከ197 በሚበልጡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ላይ ለመሰመራት ፍቃድ የወሰዱበት ሂደት ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳደግ የተሰራውን ስራ ያሳያልም ብለዋል።
የውጭ ዕርዳታና ብድርን አሰባስቦ የልማት ግቡን ከግብ ለማድረስም የተለያዩ ስራዎች እንደተሰሩ ገልጸዋል።

በዚህም ከቻይና፤ አሜሪካ፤ ሳውዲ አረቢያ መንግስታት እንዲሁም የአፍሪካና ዓለም ባንክን ከመሳሉ ተቋማት አንድ ቢሊየን ዶላር ዕርዳታና ብድር ማግኘት እንደተቻለ ጠቅሰዋል።

ቀጠናውን በማተራመስ በኢትዮጵያ ላይ የሽብር ድርጊት ለመፈጸም በሚንቀሳቀሰው የኤርትራ መንግስት ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል የተደረገው እንቅስቃሴም ውጤታማ እንደሆነ መናገራቸውን ፋና ዘግቧል።

Visitors Counter

mod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_counter
mod_vvisit_counterToday12026
mod_vvisit_counterYesterday69768
mod_vvisit_counterThis week254003
mod_vvisit_counterLast week281452
mod_vvisit_counterThis month1129565
mod_vvisit_counterLast month1271595
mod_vvisit_counterAll days( since may 28, 2013)13535655

We have: 382 guests, 40 bots online
No: 54.83.230.137
 , 
Today: Jul 31, 2014