የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አረንጎዴ አሻራ መርኃ ግብር አካሄደ

ሐምሌ 6/2014 (ዋልታ) የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የአረንጎዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካሄዱ።
 
ተቋማቱ በዛሬው ዕለት በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ነው የችግኝ ተከላውን ያከናወኑት።
 
የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ በክረምቱ መርኃ ግብር በአዲስ አበባ እና አማራ ክልል ፍኖተ ሰላም የችግኝ ተከላውን እንደሚያከናውን ጠቁመዋል፡፡
 
ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን በመንከባከብ ለዛፍነት እንዲበቁ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። በሚልኪያስ አዱኛ ለፈጣን መረጃዎች፦ ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured ቲዊተር https://twitter.com/walta_info አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!