የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞሴፔ በኢትዮጵያ የካፍ ልህቀት ማዕከልን ጎበኙ

ሐምሌ 6/2014 (ዋልታ) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኙት የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞሴፔ በኢትዮጵያ የካፍ ልህቀት ማዕከልን ጎበኙ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በፌዴሬሽኑ ባለቤትነት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን የካፍ የልህቀት ማዕከልን መጎብኘታቸውን የፌዴሬሽኑ መረጃ አመላክቷል።

የማዕከሉን የተለያዩ ክፍሎች እና የልምምድ ሜዳ እንዲሁም የፌዴሬሽኑ መለስተኛ ትጥቅ ማምረቻን የተመለከቱ ሲሆን በተመለከቱት ነገር መደሰታቸውን ገልፀዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW