ኮርፖሬሽኑ በባቡር እንዳስትሪው ዓቅም ግንባታ ላይ ማተኮሩን አስታውቀ

ኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በባቡር ኢንዳስትሪ ዓቅም ግንባታ ላይ በማተኮር እየሰራ መሆኑን አስታወቀ ።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ኢንጂነር ጌታቸው በትሩ ከ2 ሺ 500 በላይ ወጣቶችን በውጭና በውስጥ አገር በማስልጠን ስራውን እያስኬደው መሆኑን ገልጸዋል።

በዚሁም መሰረት በባቡር ምህንድስና በድህረ ምረቃ ኢንጅነሪንግ በሩሲያ በቻይና እና በእንግሊዝ ከ50 በላይ ወጣቶችን በማስተማር ዛሬ በኮርፖራሽኑ ውስጥ ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ እንዲደርሱ ማድረግ ተችለል ።

በተለያዩ የሀገር ውስጥ ዩኒቨርሲቲዎችም በተለይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመግባባት እስከ 500 የድህረ ምረቃ የባቡር ኢንጂነሪንግ ተመርቀው ገብተዋል ብለዋል።

በተመሳሳይ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር በመቀናጀት ከ600 በላይ ወጣት ቴክኒሺያኖችን መሰልጠናቸውን ነው ያመለከቱት ።

በቀላል ባቡር የሚሰሩም 254 ወጣቶች በውጭ አገር ከ500 በላይ የሚሆኑ ደግሞ በአገር ውስጥ በአጭርና በረጅም በማሰልጠን ከውጭ አገር ባለሙያዎች ጋር ልምድ በመቅሰም አሁን በመተባበር በመስራት ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

የባቡር ነጂዎች 130 የሚሆኑ ሙሉ በሙሉ በዓለም አቀፍ መስፈርት ተመርቀው ስራውን የሚሰሩ ኢትዮጵያመሆናቸውን አስታውቀዋል ።

የአዲስ አበባ ጁቡቲ መስመር በተመሳሳይ ሁኔታ ስራ ሲጀምር እስከ 2ሺ 2000 ኢትዮያውያን ማናጀሮችና ኦፕሬተሮችን ይዞ እንደሚጀምር አስታውቀዋል ።

እነዚህም  ባቡር መሰረተ ልማት ጥናት በድልድይ በዋሻዎች ግባታ በባቡረ ሃዲደ ግንባታ በኤሌከትሪክ ስራ በሌሎችም ሙያዎች ከፍተኛ ዓቅም መገንባት መቻሉን አስረድተዋል።  

የአዋሽ ወልዲያ 390 ኪሎሜትር 50 በመቶ በላይና እንደዚሁም ከመቀሌ ወልዲያ 260 ኪሎ ሜትር 40 በመቶ በላይ መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል ።

እንዚህም ዋንኛ አስቸጋሪ ስራው እየተገባደደ በመሆኑ በ2018 እ ኤ አ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንደሚውሉ መጠቆማቸውምን የዋልታ ዘገባ ያመለክታል ።  