ምክር ቤቱ ለተወዳዳሪነትና ሥራ ፈጠራ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መራ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ መንግሥትና ዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለተወዳዳሪነትና የሥራ ፈጠራ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውለውን ተጨማሪ የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በዛሬ ዕለት ለቋሚ ኮሚቴ መራ  ።      

ምክር ቤቱ  በዛሬው ዕለት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ መንግሥት  ለተወዳዳሪነትና የሥራ ፈጠራ  የሚውለውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በአግባቡ መርምሮ ነው ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንዲመራ ያደረገው  

የብድር ስምምነቱ ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙትን የቦሌ ለሚ ሁለት እና የቂሊንጦ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ግንባታ ለማስጨረስ እንደሚውልም ታውቋል፡፡

በተለይ ደግሞ ለፓርኮቹ ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ በተሟላ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የሚያግዝ የአንድ መቶ ሰባ አምስት ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ብድር ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደው ምክር ቤቱ የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ መስከረም 28 ቀን ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበ የድጋፍ ሞሽን አድምጧል፡፡