ኢትዮጵያ ከባህረ ሰላጤው ሀገራት ጋር የኤሌክትሪክ ኃይል አቀርቦት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመች

ኢትዮጵያ ገልፍ የኤሌክትሪክ ትስስር ከተባለ የባህረ ሰላጤው አባል ሀገራት ጋር የኃይል አቀርቦት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመች፡፡

የኢፌዴሪ ውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ገልፍ የኤሌክትሪክ ትስስር ከተሰኘ ተቋም እና ከዓለም አቀፉ የኃይል አቅርቦት ድርጅት ጋር የኃይል አቅርቦትን መሠረት ያደረገ ጥናት ለማካሄድ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ነው የተፈራረሙት።

በመግባቢያ የስምምነት ፊርማ ስነ ሥርዓት ላይም የኢፌዴሪ የውሃ፣ መስኖና ኤለክትሪክ ሚኒስትር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ፣ የባህረ ሰላጤው የኤለክትሪክ ትስስር ባለሥልጣን ሥራ አስፈፃሚ አህመድ አል ኢብራሂምና የዓለም አቀፉ የኃይል ትስስር ድርጅት ሊቀመንበር ሊዮ ዚኒያ ተገኝተዋል፡፡ 

በአትዮጵያና በባሀረ ሰላጤው ሀገራት መካከል ወደፊት በሚኖረው የሃይል ትስስር የአዋጭነት ጥናት የስምምነቱ አካል መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ስምምነቱ በባህረ ሰላጤው አካባቢ ያለውን የኃይል አቅርቦት ከማሻሻሉም በተጨማሪ የአካቢውን የኃይል ደህንነት በማሳደግ በኤሌክትሪክ ሥርዓቱ ላይ መተማመንን ሊፈጥር የሚችል ነው ተብሏል፡፡ (ኤፍ.ቢ.ሲ)