የፌዴራል ሥርዓት የግጭት መንስዔ እንደማይሆን አፈ ጉባዔው ገለፁ

በህዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተው የፌዴራሊዝም ሥርዓት የግጭት መንስዔ የሚሆንበት ምክንያት እንደሌለ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አስታወቁ፡፡

በአንዳንድ አካላት አገሪቱ የምትከተለው የፌዴራል ሥርዓቱ ለግጭት መንስዔ እየሆነ ነው በሚል የሚናፈሰው  ወሬ ከእውነታ የራቀ እንደሆነ አፈ ጉባዔ ያለው አባተ ለዋልታ ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል ሥርዓቱ በህዝቦች መካከል ከግጭት ይልቅ መተሳሳብን፣ መቻቻልና መቀራረብን በመፍጠር የተሻለ ሥርዓት እንዲዘረጋ ማስቻሉን አፈ ጉባዔው አስገንዝበዋል፡፡

አገሪቱ በአሀዳዊ ሥርዓት ስትመራ በነበረበት ዘመን ከፍተኛ ዕልቂት እንደነበር አቶ ያለው አስታውሰው የፌዴራል ሥርዓቱ በህዝቦች መካከል መቻቻልና መተሳሰብ እንዲሰፍን አስችሏል ብለዋል፡፡

ኢህአዴግ አገሪቱን ከመቆጣጠሩ በፊት ከ10 በላይ ድርጅቶች መሳሪያ ታጥቀው ወደ ትግል ገብተው እንደነበር አፈ ጉባዔው ይናገራሉ፡፡ ይህም አሀዳዊ ሥርዓቱ ምቹና የዜጎችን መብት ያላከበረ በመሆኑ ለውጥ ናፋቂዎችን አስነስቷል ይላሉ፡፡

ግጭት በተለያዩ ምክንያቶች ሊነሳ እንደሚችል የጠቆሙት አቶ ያለው ድብቅ ዓላማ ያላቸው አንዳንድ አካላት የፌዴራል ሥርዓቱን እንደ መንስዔ ለመጠቆም መሞከራቸው ፍፁም ተገቢነት የለውም ብለዋል፡፡

የፌዴራል ሥርዓት የግጭት መንስዔ ቢሆን ኖሮ ሥርዓቱን የሚከተሉት እነ አሜሪካ፣ህንድና ስዊዘርላንድ ወደ ግጭት ባመሩ ነበር ሲሉም በማሳየነት ይጠቅሳሉ፡፡

ሰሞኑን በአማራ ክልል የተከሰተው ግጭት ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው አፈ ጉባዔው ተናግረዋል፡፡ የማንነት ጥያቄው ህግና ሥርዓትን ተከትሎ የሚቀርብበት አካሄድ መኖሩን ጠቁመው ህጋዊ ጥያቄውን ሽፋን በማድረግ ሌላ ተልዕኮ ለማስፈፀም የሚንቀሳቀሱ አካላት ግጭት እንዲፈጠር አድርገዋል ብለዋል፡፡

መንግስት የመልካም አስተዳር እጥረት ችግሮችን በየደረጃው ለመፍታት ቆርጦ በመነሳት ወደ ተግባር መግባቱን አቶ ያለው አስረድተዋል፡፡ ህዝቡም ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ችግሮች መፍትሔ እንዲያገኙ የሚጠበቅበትን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ጥያቄዎችንም በህጉ መሰረት በሠላማዊ መንገድ በማቅረብ ተገቢው ምላሽ እንዲሰጠው ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ የፌዴራል ሥርዓቱን በመጠበቅና በማስከበር በኩል ሁሉም የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገገባም አቶ ያለው ጨምረው ገልፀዋል፡፡