ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲፕሎማቶች ጋር እየተወያዩ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲፕሎማቶች ጋር በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ ዲፕሎማት ዓለም አቀፋዊ አዝማሚያዎችን በመረዳት በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ላይ የተመሰረተ ሀሳብና አሠራር መመስረት አስፈላጊ መሆኑን በአጽንዖት ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ዲፕሎማቶች የመንግስት ፖሊሲን የመተግበር፣ የሚመደቡባቸውን አገራት ፖሊሲ የመገንዘብ እና በአገራቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መብት የማስጠበቅ ሚና እንዳላቸው አስታውሰዋል።

ውይይቱም በሚኒስትር መስሪያ ቤቱና በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ውስጥ የተደረጉትን ለውጦች ለመገምገም ያቀደ ነው ተብሏል፡፡ (ምንጭ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)