ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማቡዛን ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማቡዛን ተቀብለው አነጋገሩ ።    

ውይይቱም በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነትና ትብብር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ  የሚያተኩር  እንደሆነ  ተገልጿል ።

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሴሪል ራምፓሳ በዘንድሮ ዓመት ህዳር ወር ላይ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው  ይታወሳል  ።

በዛሬው  ዕለት  የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፖከ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ  ጋር  ያደረጉት  ውይይት ከፕሬዚዳንት ሴሪል ጋር የተደረገው  ውይይት ቀጣይ ክፍል በመሆኑ ተገልጿል ።