አመታዊ የአምባሳደሮች ስብሰባ እየተካሄደ ነው

ኢትዮጵያን በውጭ ሀገራት የሚወክሉ አምባሳደሮች፣ ቆንስላ ጄኔራሎች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጄኔራሎችና ዳይሬክተሮች የተሳተፉበት አመታዊ ኮንፈረንስ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

ለአንድ ሳምንት የሚቆየው ይህ ኮንፍረንሱ የዋናው መሥሪያ ቤት እና በውጭ የሚገኙ ሚሲዮኖች የስራ እንቅስቃሴና ተግዳሮቶች እንዲሁም ክልላዊና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች በኢትዮጵያ እና በጎረቤት አገራት ላይ በሚያሳድረው ተፅዕኖ ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ ይወያያል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ኮንፈረንሱ በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ፣ በዜጎችና በዳያስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ በአሁኑ ውቅት በውጭ አገራት በ45 ኤምባሲዎችና በ13 ቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤቶች እንደምትወከል የውጭ ጉዳይ መረጃ ያሳያል፡፡ (ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት)