የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

 የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል።

ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የድርጅትና የመንግስት የስራ አፈጻጸም እንዲሁም በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ላይ ሲሆን አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

እንዲሁም በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈጻጸምን ይገመግማል ነው የተባለው፡፡

በስብሰባው በመስከረም ወር በሐዋሳ በተካሄደው በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የአጋር ፓርቲዎች ሊቀመናብርትና ምክትል ሊቀመናብርት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡   ምንጭ፡-(የኢህአዴግ ፅህፈት ቤት)