ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በኬንያ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አወገዙ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኬንያ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አወገዙ።

 ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመዲናዋ ናይሮቢ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በመንግስታቸው ስም አውግዘዋል።

 ለተጎጅ ቤተሰቦችና ለመላው ኬንያውያንም መፅናናትን እንደተመኙ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ለኬንያ ህዝብና መንስግስት መፅናናትን የተመኙ ሲሆን ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ከኬንያ ጎን እንደምትሆን አስታውቀዋል፡፡

 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁም በትናትናው ዕለት በኬንያ የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት በፅኑ አውግዘዋል፡፡

 ትናንት በናይሮቢ በሚገኝ ዘመናዊ ሆቴል በተፈጸመ ጥቃት 15 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።

 ምንጭ ፡-(የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)