መንግሥት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ ምሁራን ገለጹ

በአገሪቱ  የተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶችና ሁከቶችን ለመቆጣጣር መንግሥት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ  እርምጃዎችን ሊወስድ እንደሚገባ  ምሁራን ገለጹ ።

ምሁራን  እንደገለጹት በተለያዩ ቦታዎች እየተባባሱ የመጡትን  ግጭቶችና ሁከቶችን ለማስቆም  ተገቢው  ህጋዊ  እርምጃ  መውሰድ  እንዳለበት በጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት አቶ ዘላለም የኔነህና በተለያዩ  ዩኒቨርስቲዎች መምህር የሆኑት ""ዶክተር  ንጋት አስፋው  ተናግረዋል ፡፡

በግጭቱ ምክንያትም ሰዎች እየሞቱና ብዙ ንብረት እየወደመ ነዉ ያሉት ዶክተር ንጋት በሃገሪቱ ለዉጥ እንዳለ ሆኖ ነገር ግን  በጎጥ በመደራጀት   ሁከት  የመፍጠር ሁኔታ  እየተበራከተ  መምጣቱን  ተናግረዋል ።

በሃገሪቱ ዉስጥ ያለዉ ለዉጥ እንዳለ ሆኖ አሁን የተነሱት የማንነት ጥያቄዎች መንግስት በተገቢዉ መሠረት መፍታት አለበት ሕብረተሰቡም ጥያቄዉን ሲያቀርብ ሕጉንና ሕግ መሠረት አድርጎ መጠየቅ እንዳለበት ሙሁራን ያሳስባሉ፡፡

 "መንግስት ጥርስ እንዳለዉ መንከስ እንደሚችልና አስፈላጊም ከሆነ  የኃይል እርምጃ መውሰድ  እንደሚችል ማሳየት "ማሳየት አለበት ብለዋል ፡፡

የጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት አቶ ዘላለም የኔነህ በበኩላቸው እንዲት እርግብ በመያዝ (የእርግብ ምስል)፤ ነጭ ባንዲራ በማዉለብለብ ሰላም ማምጣት አይቻልም ይልቁንስ ሰላምን ለማምጣት ችግሩን ከሥረ መሠረቱ የመፍታት ሥራ ማከናወን  እንደሚያስፈልግ ገልጿል ፡፡

የተጀመረዉን ለዉጥ ለማስቀጠልና እዛም እዚም የሚከሰተዉ ችግር መንግስት መፍታት ካልቻለና  ሕብረተሰቡም  ሊተባበር ካልፈቀደ መጨረሻዉ ህልውናቸው አደጋ ላይ ከወደቁ  የአለም ሀገራት ሊሆን እንደሚችል አቶ ዘላለም አሳሰበዋል፡፡

ሁለቱም ሙሁራን በአገር አቀፍ ደረጃ ለዉጥ ሊመጣ የሚችለዉ ሁሉም የበኩሉን የድርሻዉ መወጣት ሲችል ነዉ ብለዋል፡፡