ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት የሚወክሉ ዲፕሎማቶች የተሰጣቸውን ሀላፊነት ለመፈፀም በትጋት መስራት ይኖርባቸዋል- ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ

ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት ወክለው የሚመደቡ ዲፕሎማቶች ሀገርን ወክሎ እንደመስራት ያለ ትልቅ ነገር እንደሌለ በመገንዘብ የተሰጣቸውን ሀላፊነት ለመፈፀም በትጋት መስራት እንዳለባቸው ክብርት ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ አሣሠቡ፡፡

ለአንድ ሳምንት ሲካሄድ የነበረውን የኢትዮጵያዊያን አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ስብስባ መጠናቀቁን በማስመልከት ትናንት ምሽት በብሔራዊ ቤተ-መንግስት የእራት ግብዣ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡

“በልባችሁ ይዛችኋት የምትሔዷት ኢትዮጵያ ብዙ እንዲሰራላት የምትጠብቅ ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ ለዓለምም ሆነ ለቀጠናው ሰላም መረጋገጥ የሚጠበቅባትን በማድረግ ጉልህ ምሳሌ ናት፡፡

ይህንንም አስጠብቆ ለመቀጠል በበለጠ ትጋትና ጥንቃቄ መስራት ይኖርባችኋል፤” ብለዋል ፕሬዘደንቷ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ ሀገራት የሚኖረውን ዲያስፖራ በማቀናጀት ለኢትዮጵያ ልማት እና እድገት አስተዋፅኦ ማድረግ የሚችልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ሁነኛ ስራቸው ሊሆን እንደሚገባ አሣሥበዋል፡፡/መረጃውን የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አድርሶናል፡፡