ቀዳማዊ እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በሽረ እንዳስላሴ ለሚገነባ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሠረተ ድንጋይ አስቀመጡ

ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በሽረ እንዳስላሴ በ20 ሚሊንዮን ብር የሚገነባ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሠረተ ድንጋይ አስቀመጡ ።     
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በሽረ እንዳስላሴ ከተማ በ20 ሚሊዮን ብር የሚገነባ የ2ኛ ደረጃት ቤት መሠረተ ድንጋይ አስቀመጡ፡፡
በዛሬው ዕለት በሽረ እንዳስላሴ ከተማ በቀዳማዊ እመቤቷ የመሠረተ ድንጋዩ የተቀመጠው የ2ኛ ደረጃ የትምህርት ቤት ግንባታ 20 ቢሊየን ብር ወጪ በኢፌደሪ ቀዳማዊ እመቤት ጽህፈት ቤት እንደሚሸፈን ታውቋል፡፡  
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ዛሬ ረፋዱ ላይ ሽረ ከተማ ሲደርሱ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የከተማው ነዋሪ ህዝብ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ በሽረ እንንዳስላሴ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡(ምንጭ :ቀዳማይ እመቤት ጽህፈት ቤት)