የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ በ5 ሚሊዮን ብር ሊከናወን ነው

በ5 ሚሊየን ብር ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ሊከናወን ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ5 ሚሊየን ብር ወጪ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ሊያከናውን ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር በመሆን ማዕከሉን እየጎበኙ ሲሆን÷የውስጥ ለውስጥ የአስፓልት ግንባታው በዛሬው እለት በይፋ ተጀምሯል፡፡

መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ነው።