37ኛው የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኞች መደበኛ ስብሰባ ተጀመረ

37ኛው የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኞች መደበኛ ስብሰባ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

በስብሰባው ስደተኞችና ከስደት ተመላሾችን በሚመለከት ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድ ተጠቁሟል ።

በአፍሪካ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰቱ ባሉ ግጭቶች ምክንያት  የሚደርሱ  የዜጎች መፈናቀል ችግሮች ለመፍታትና ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ምክክር እንደሚካሄድም ታውቋል፡፡ 

በውይይት መድረኩ የተለያዩ ሪፖርቶች ቀርበው በህብረቱ ቋሚ መልዕክተኞች ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል፡፡

ቋሚ መልዕክተኞቹ በ32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የሚቀርብ የውሳኔ ሃሳብ እንደሚያቀርቡም  ተገልጿል።

የውሳኔ ሓሳቡ በወሩ መጨረሻ በሚካሄደው 34ኛው የሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ቀርቦ በሥራ አስፈጻሚዎቹ ከፀደቀ በኋላ ለመሪዎች ጉባኤ የሚቀርብ ይሆናልም ተብሏል።

32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በቀጣዩ ወር መጀመሪያ ይካሄዳል።

ይህ ስብሰባ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነትን እየመራች ባለችው ሩዋንዳ የሚዘጋጅ የመጨረሻ ስብሰባ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡