በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ በደረሰው የቦምብ ጥቃት በትንሹ 11 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

አልሸባብ ሃላፊነቱን በወሰደበት በዚህ ጥቃት ፍንዳታው በደረሰበት የናይኖቢው ቅንጡ ሆቴል ምርምራዎች ተጠናክረው እየተካሄዱ ነው ተብሏል፡፡

በኬኒያዋ መዲና ናይሮቢ በቅንጡ ሆቴል ተቀነባብሮ ትናንት በደረሰው የቦምብ አደጋ በርካቶች ቆስለው ሆስፕታል ሲገቡ በተቀነባበረው ሴራ ህይወታቸው የተቀጠፉም በርካቶች መሆናቸው እየተዘገበ ይገናል፡፡ ሲኤንኤን በትንሹ 11 ሰዎች በትናንቱ የናይሮቢ አደጋ ህይወታቸው ተቀጥፏል ሲል ዘኢንዲፐንደንት ደግሞ የሟቾቹን ቁጥር 15 ያደርሰዋል፡፡

በናይሮቢው ደሲት ዲቱ የተባለ ቅንጡ ሆቴል ተቀነባብሮ ለደረሰው የሽብር ጥቃት እስላማዊ ቡድን ነኝ የሚለው አክራሪው አልሻባብ ድርጊቱ በታጣቂዎቼ ተቀነባብሮ የተፈጸመ ነውና ኃላፊነቱን እኔ እወስደዋለሁ ነው ያለው ።  

አልሸባብ በመግለጫው ታጣቂዎቹ ከማክሰኞ ጀምሮ በሆቴሉ ላይ ከትሞ ከ24 ሰዓታት በላይ በዚያ እንደነበሩም ነው ያስታወቀው፡፡ 

እንደ ኬኒያ ፖሊስ ዘገባ ደግሞ ጥቃቱ የተጀመረው ተሸከርካሪዎች ቆሞ ከነበሩበት ሥፍራ ሲሆን የቦምብ ፍንዳታው የበርካቶችን የሆቴሉ እንግዶች ህይወት ልቀጥፍ የቻለው በመውጣት ላይ እያሉ ነው ተብሏል፡፡

የኬኒያ የሃገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር እንዳስታወቀው እስከትናንትናው እኩለ ለሊት ሙሉ ህንጻው ላይ አደጋ በመድረሱ ሰዎች ከሆቴሉ እንዲወጡ አድርጓል፡፡

ማክሰኞ በደት ዲቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ በአልሸባብ ታጣቂዎች በተቀነባበረው በዚህ የሽብር ድርጊት ላይ በምስራቅ አፍሪካ እውቅ የሽብር መሪ አካላቱ ተሳታፊ እንደነበሩም ሲኤንኤን በዘገባው ያስረዳል፡፡

እንደ የኬኒያ ባለስልጣናት ዘገባ ከሆነም መላው ሆቴሉ ሰራተኞች እና የውጭ ሀጋራት እንግዶች ሆቴሉን ለቀው እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን በጸጥታ አካላቱ ጥበቅ ምርመራ እና ጥበቃ በስፍራው እየተደረገም ይገኛል፡፡

ሲ ኤን ኤን የሆቴሉን ሰራተኛ በምንጭነት ጠቅሶ እንደ ዘገበው በሆቴሉ መውጫ በር ላይ ስድስት አስከረኖች የተገኙ ሲሆን በሆቴሉ ጀርባ ባለው መዝናኛ ስፍራም ተመሳሳይ ቁትር ያለው የሟቾች አስከረን መገኘቱን ተረድቷል፡፡ የኬኒያ የጸጥታ አካላቱ ምናልባትም የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ እንደምችል ነው እየተናገሩ ያሉት፡፡ ናይሮቢ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ይፋ እንዳደረገው ከሟቾቹ መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያለው ሟች ተገኝቶበታል፡፡

የጸጥታ አካላቱ በበኩላቸው ለጥፋቱ ሃላፊነቱን የሚወስደው አልሸባብ መሆኑን አረጋገትኩ ብሏል፡፡

እሮብ በሆቴሉ አደጋው በተከሰተ ጊዜ ለመዝናናት ሲሉ በስፍራው የታደሙ ወዳጆች በደረሰው አስከፊ አደጋ ሲያለቅሱና ሲረበሹ ተስተውሏል፡፡ የሀገሪቱ ቀይመስቀልም ከአደጋው በኋላ ተጎጂዎቹን ለመርዳት ሲሯሯጥ ታይቷል፡፡

ከአደጋው ባሻገርም የተጋነኑ ሃሰተኛ ምስሎች ልወጡ ይላሉ ያለው የኬኒያ ፖሊስ ኬኒያውያኑ ነዋሪዎችን ከሚረብሹ የሃሰት ዜናዎች ስርጭት እንድቆጠቡ አሳስቧል፡፡

የኬኒያ ብሄራዊ ፖሊስ አገልግሎት ጠቅላላ ኢንስፔክተር ጆሴፍ ቦኔት, አጥፊዎቹ ስራቸውን የጀመሩት ማክሰኞ እንደመሆኑ በሆቴሉ ሰዎች የሚበዙበት ስፋራዎች አስቀድሞ የተጠኑ ነበርና አደጋው አስከፊ ሆኗል ነው ያሉት፡፡

በአደጋው አደገኛ የጦር መሳሪዎች በጥቅም ላይ የዋሉ በመሆኑ በአየር ላይ እየተሸከረከረ ካለው ሄሊኮብተር ውጭ በስፍራው ያሉ ተሸከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱና የሆቴሉ ሰራተኞች ሊከሰት የሚችለውን ተጨማሪ ፍንዳታ እንዲሸሹ እንዲሸሱ ታዟል፡፡

በአደጋው የተረበሹ የአከባቢው ነዋሪዎች እና አደጋው የደረሰባቸው እንዲሁም  በአከባቢው የናይኖቢ ዩንቨርሲቲ ቺሮሞ ካምፓስ ተማሪዎች በድንጋጤ ስፍራውን ጥለው በጎዳናው ሲሸሱም ታይተዋል፡፡

ከፍንዳታው በኋላ ቀጥተኛ በንጹሃን ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ ተኩሶች እንደነበሩም ከናይሮቢ ለሲኤን ኤን  የሚዘግበው ኢቫንስ , ያብራራል፡፡
አደጋውን ተከትሎም ዓለማቀፉ ማህበረሰብ በአልሸባብ ላይ ውግዘት እያቀረቡ ነው፡፡

በኬኒያ የአሜሪካው አምባሳደር ቦብ ዴግ በኤምባሲያቸው ላይ ምም አይነት አደጋ እንዳልደረሰና ሰራተኞቻቸውም ደህና መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የተመድ ዋና ጸሃፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ  ደርጊቱን በመቃወም ከኬንያውያኑ ጋር መሆናቸውንና ከኬኒያ መንግስት ጋር እንደንሰሩም ነው ያስታወቁት፡፡

ኬኒያን አሁን የገጠናት የሽበር አደጋ ከ6 ዓመታት በፊት በዌስት ጌት የገበያ ማዕከል በአልሻባብ አቀነባባሪነት በተደገሰው የ67 ሰዎች ህልፈት ጋር እየተነጻጸረም ነው፡፡  አልሻባብ በኤልዲ  ወታደራዊ ጣቢያ 140 የኬኒያ ወታደሮችን ህይወት ከቀጠፈም እነሆ በእለተ ማክሰኞ ሶስተኛ ዓመቱን የምደፍንበት እለት ነበርና ጥፋቱ በሰፊው የታሰበበት መስሏል፡፡