በኢትዮጵያ ታክስ መክፈል ካለበት የህብረተሰብ ክፍል ውስጥ 60 በመቶው ብቻ ታክስ እየከፈለ እንዳለ የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
ይህ የተገለጸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሰራተኞቹ የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ ባዘጋጀበት ወቅት የገቢዎች ሚኒስትሯ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከጋዜጠኖች ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው፡፡
የታክስ አሰባሰብ ሂደቱ ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመፍታት የገቢ አሰባሰብን ለማዘመን ታህሳስ 12 2011 ዓ.ም የተከፈተውን ሀገራዊ የታክስ አሰባሰብ ንቅናቄ ስኬታማ እንደሆነ ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡