የጤናማ እናትነት ወርን ምክንያት በማድረግ በጤና ሚኒስቴር የደም ልገሳ ፕሮግራም ሊከናወን ነው

የጤናማ እናትናት ወርን ምክንያት በማድረግ የጤና ሚኒስቴር የደም ልገሳ  ፕሮግራም ሊያከናውን መሆኑ  ተገለጸ ።

የጤናማ እናትነት ወርን ምክንያት በማድረግ በመጪው ሰኞ እና ማክሰኞ (13-14/2011ዓ.ም) ለጤና ሚኒስቴር ሠራተኞች የደም ልገሳ ፕሮግራም እየተዘጋጀ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሣ ገልፀዋል ።

ሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶችም ተመሳሳይ ፕሮግራም በማዘጋጀት ሠራተኞቻቸው እናቶችን ለመታደግ ደም መለገስ እንዲችሉ እንዲደረግ ዶ/ር ተገኔ ጥሪ አቅርበል ።(ምንጭ:  የጤና ሚኒስቴር)