በሰውነት ሙቀት ቻርጅ የሚደረግ ስማርት የእጅ ሰዓት ተሠራ

በሰውነት ሙቀት ቻርጅ የሚያደርግ ስማርት የእጅ ሰዓት መሠራቱ ተገለጸ ።

በተለይ ደግሞ በቀላሉ ሰዎች በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በቀላሉ ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ ምቹ የሆኑ ስማርት የእጅ ስልኮችን ጨምሮ አዳዲስ አገልግሎቶችን የሚሠጡ ስማርት የእጅ ሰዓቶች ስሪት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል፡፡

ቀደም ሲል የተለያዩ አገልግሎት የሚሠጡ ስማርት እጅ ሰዓቶች ተሠርተው ለገበያ ቀርበዋል፡፡

አሁን ተሠራ የተባለውና ከሰውነት በሚገኘው ሙቀት ብቻ ቻርጅ ማድረግ የሚችል ስማርት የእጅ ሰዓት መሠራቱን ከሲኤን ኤን የተገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

ይህ የእጅ ሰዓት ምንም አይነት ባትሪ መጠቀም ሳያስፈልግ በሰውነትዎ ቢያገኘው ሙቀት ብቻ ጃርጅ በማድረግ ይሠራል ነው የተባለው፡፡ 

ቀደም ሲል የተሠሩት ስማርት የእጅ ሰዓቶች ምንም እንኳን የተለያዩ አገልግሎት የሚሠጡ ቢሆንም  ይህ ስማርት የእጅ ሰዓት በውስጡ በተገጠሙለት አነስተኛ ተሸከርካሪ መሣሪያዎች አማካኝነት አሰቱን ባትሪ ቻርጅ የሚያደርግ ሙቀት እንዲመጭ ያደርጋሉ፡፡

ይህ ስማርት የእጅ ሰአት በዉስጡ በተገጠሙለት አነስተኛ የሚሽከረከሩ መሣሪያዎች አማካኝነት ሰዓቱን ባትሪ ቻርጅ የሚያደርግ ሙቀት እንዲመነጭ ያደርጋሉ፡፡ 

ይህ ማትሪክስ ፓወር ተሰኘ ሰዓት ቻርጅ የአለማችን የመጀመሪያው  ቻርጅ  ማድረግ የማይፈልግ በእጅዎ ካጠለቁት ብቻ የሚሰራ ሰአት ነዉ፡፡

ይህ ሰአት ከዚህ በተጨማሪ አንድ ሰው በቀን ዉስጥ ምን ያህል ካሎሪ እንዳቃጠለ እና ምን ያህል ኤሌክትሪክ ሃይ ባን ውስጥ ማመንጨት እንደቻለ በአጠቃላይ ሰአት ላይ ያሳያል ነው የተባለው፡፡

ሌላዉ ይህ ፓወር ዋች አ ፕል ስማርት ሰአት እስከ 200 ሜትር ጥልቅት ውሃን ዘልቆ የማይገባበት ከመሆኑም ባሻገር ለሁለት አመት ያህል ከእጅ እስካልወለቀ ድረስ ያለምንም ባትሪ ከሰዉነት በሚመነጨዉ ሙቀት ብቻ ቻርጅ እያደረገ መስራ የሚችል የመጀመሪያዉ ስማርት የእጅ ሰአት ሆኗል፡፡ 

አሁን የተሰራው ይህ ስማርት ሰዓት በተለይም ደግሞ እስከአሁን የተሰሩት ስማርት የእጅ ሰአቶች የሚገጥማቸውን የባትሪ ችግር እንደሚቀርፍም ተገምቷል፡፡

ይህ ስማርት አይፎን የእጅ ሰአት እንደ ስልክም በተጨማሪ የስልክ አገልግሎትም ይሰጣል ነዉ የተባለው፡፡