የአፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት በኢትዮጵያ ሊዘጋጅ ነው

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢኖቬሽን ቢዝነስ አክስለሬሽን ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የአፍሪካ የኢኖቬሽን ሳምንት ከጥቅምት 17 እስከ 21፤2012 ለማካሄድ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

የኤግዚብሺኑ ዋና ዓላማ ወጣቶችን ብሎም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደረጉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ማስተዋወቅና ወደ ስራ እንዲገቡ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ነው ተብሏል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የኢኖቬሽን ሳምንቱ መዘጋጀት ሚኒስቴሩ ለያዘው የቴክኖሎጂ የስራ ፈጠራ ሥራ አጋዥ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

የአይ ቢ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ሙሉጌታ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የኢኖቬሽን ሳምንት ለሴቶች ልዩ ትኩረት ተሠጥቶ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በዚህ ስራ ተሳታፉ ሲሆኑ የስራ አጥ ቁጥር መበራከት እንደሚያሳስባቸው ገልፀው ይህንን ችግር ለመቅረፍ ቴክኖሎጂን ማበልፀግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሰራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ (ምንጨ፡-የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር)