ኢንቨስተሮች የሚሠማሩባቸው መስኮች ቢያንስ 25 በመቶ ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ መሆን አለባቸው

ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ኢንቨስተሮች የሚሠማሩባቸው መስኮች ቢያንስ 25 ከመቶ የአገር ውስጥ  እሴትን የሚጠቀሙና ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ መሆን አለባቸው ። ዶክተር እንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ።   

‹‹ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ኢንቨስተሮች የሚሰማሩባቸው መስኮች ቢያንስ 25 ከመቶ የሀገር ውስጥ እሴት የሚጠቀሙ፤ ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩና የተማረ የሰው ሃይል የሚፈልጉ ዘርፎች ላይ እንዲሆኑ አምባሳደሮች መሥራት አለባቸው፡፡›› የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ  ሚንስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ተናግረዋል ።

ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት ለወከሉ አምባሳደሮች ኢኮኖሚውን በቴክኖሎጂ መደገፍ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡