ቋሚ ኮሚቴው በተለያዩ ጉዳዩች ላይ እየመከረ ነው

ሐምሌ 6/2014 (ዋልታ) የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የሁሉም የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች በተገኙበት በተለያዩ ጉዳዩች ላይ እየመከረ ነው፡፡

ለኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ዘርፈ ብዙ ግልጋሎት እየሰጠ የሚገኘው የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ በክልሎች መካከል ውጤታማና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልን ለማረጋገጥ የሚረዳ የፌዴራል ድጎማና የጋራ ገቢዎች ቀመር እንዲዘጋጅ በማድረግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም ኮሚቴው የማከፋፈያ ቀመሮቹ በፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልና በክልሎች የተመጣጠና እድገት ላይ ያላቸውን አንድምታ እንዲጠና በማድረግ እና የውሳኔ ሀሳቦችን ለምክር ቤቱ በማቅረብ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እንዲመዘገቡ ያለሰለሰ ጥረት ማድረጉ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የፌዴራል የመሠረተ ልማት አውታሮች ስርጭት ፍትሃዊ እንዲሆኑ የሚረዱ የአሰራር ሥርዓቶችን እየዘረጋ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው፡፡

በዚሁም መሰረት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የ2014 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ሁሉም የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት እየመከረ መሆኑን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW