በሕግ ማስከበር ዘመቻው የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ አበረታች ሥራ ሠርቷል – ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌ

                        ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌ

የካቲት 16/2013 (ዋልታ) – ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌ በተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ በጤናው ዘርፍ አበረታች ሥራ መሥራቱን ገልጸዋል።

የህወሃት ጁንታ ጥቃት በሰሜን ዕዝ የሠራዊት አባላት ላይ ብቻ ሳይሆን የዕዙ የጤና ተቋማት እና የጤና ሙያተኞችንም የጥቃቱ ሰለባ አድርጓል ብለዋል።

በዚህም በሕግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት በጤናው ዘርፍ ሊያጋጥም የሚችልን የሰው ኀይል እና መሰል ችግሮች የሀገርን አቅም በመጠቀም መቅረፍ መቻሉን ተናግረዋል።

የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ከጤና ሚኒስቴር እና ከአማራ ክልል ጤና ተቋማት ጋራ የሠራው የተቀናጀ ሥራ መልካም መሆኑን የጠቆሙት ሌተናል ጀኔራል ባጫ፣ ይሄም በሕግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት በህክምና እጦት እና በእንግልት ምክንያት ጉዳት እንዳይደርስ አስችሏል ብለዋል። መረጃው የመከላከያ ሚኒስቴር ነው።

 

shares