በአማራ ክልል የ247 ነጥብ 8 ችግኝ የአንድ ጀበር ተከላ ኘሮግራም እየተካሄደ ነው


ሐምሌ 15/2013 ( ዋልታ)-
በአማራ ክልል በአንድ ጀበር 15 ዞኖች፣ 157 ወረዳዎች ተሳትፈው 247.8 ሚሊየን ችግኞች ይተከሉሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ተከለው በ24 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ይከናወናል ተብሏል።
የክልሉ ርዕሰ መሥተዳደር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በባህርዳር ቤዛዊት ማሪያም አካባቢ አረንጓዴ አሻራቸውን እንደሚያሳርፍ እየተጠበቀ ነው።
በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 2 ቢሊዪን ችግኝ መትከልን ታሳቢ ያደረገ ግብ ተጥሏል።
የክልሉ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ግንቦት 30 ደብረማርቆስ ተገኝተው ማስጀመራቸው ይታወሳል::