በየቀኑ በደቡብ አፍሪካ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በ33% እያሻቀበ ነው ተባለ

 

በደቡብ አፍሪካ በየቀኑ በኮሮና ቫይረስ 33 በመቶ እያሻቀበ ሲሆን በቫይረሱ ምክንያትም የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር 390 እና በ600 መካከል እየተመዘገበ መሆኑ ተነገረ፡፡

በሀገሪቱ አዲስ በቫይረሱ እየተያዙ ያሉ ሰዎች ቁጥር ከሳምንት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በ33 በመቶ ማሻቀቡን

የደቡብ አፍሪካ የሳይንስና ኢንደስትሪያል ምርምር ካውንስል ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ሪደዋን ሱሊማን መናገራቸውን ኤስ ኤ ቢ ሲ የዜና ምንጭ ዘግቧል፡፡

እንደ ዜና ምንጩ መረጃ ከሆነ በደቡብ አፍሪካ የመመርመር አቅም እየጨመረ የመጣ ቢሆንም ዜጎች የመከላከያ ፕሮቶኮሎችን ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ምክንያት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል።

አሁን ላይ በሀገሪቱ በየቀኑ እየተመዘገበ ያለው የኮሮና ተያዦች ቁጥር ባለፉት አምስት ቀናት ከተመዘገበው የ20 ሺህ ብልጫ እንዳለው ተመራማሪው ተናግረዋል።

በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር በተመርማሪዎች ቁጥር ሁኔታ ላይ የሚመሰረት ሲሆን ከቫይረሱ የመራባት ባህሪ በተጨማሪ ሰዎች አዲስ ዓመትንና የልደት በዓልን ለማክበር መሰባሰባቸው እንደ ዋና ምክንያ ሊጠቀስ እንደሚችል ጨምረው መናገራቸውን በመረጃው ተመላክቷል።

ቀደም ሲል የዘርፉ ተመራማሪዎች የቫይረሱ በፍጥነት መተላለፍ ለአዲስ የቫይረሱ ዝርያ መፈጠር ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ገልጸው እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡

በአገሪቱ እስካሁን ከ1 ሚሊዮን 230 ሺህ ሰዎች በላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከ33 ሺህ 163 ሰዎች በላይ ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

shares