ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የሰጡት መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አለመሆኑ ተገለጸ

ግንቦት 02/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሰሞኑን የተናገሩት እና በማኀበራዊ መገናኛዎች ሲዘዋወር የነበረዉ ሃሳብ የግላቸዉ እንጅ የቤተክርስቲያኗ አቋም አለመሆኑን የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ገለጸ፡፡

በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ችግር ሲፈጠር ቅዱስ ሲኖዶሱ ተወያይቶ መግለጫ ሲሰጥ ቆይቷል፤ እየሰጠም ነው፤ እርዳታም ተደርጓል ሲሉ የተናገሩት የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ ናቸዉ፡፡

እንደ ዋና ጸሐፊው ገለጻ አቡነ ማትያስ ተናገሩት ተብሎ በማኀበራዊ መገናኛዎች የተሰራጨው ንግግር  ቅዱስ ሲኖዶሱ ያልተወያየበት እና ያልወሰነው ጉዳይ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶሱን የማይወክል ሀሳብ ነው ብለዋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶም በቀጣይ በአጀንዳ የተያዘ እና ቅዱስ ሲኖዶሱ የሚወያይበት እንደሆነ መገለጹን አሚኮ ዘግቧል፡፡