«ኢትዮጵያን ስላገለገላችሁ ኢትዮጵያ ታመስግናችኋለች» በሚል መርህ የስነ ጥበብ ባለሙያዎች የምስጋና መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

መጋቢት 30/ 2013 (ዋልታ) – “ኢትዮጵያን ስላገለገላችሁ ኢትዮጵያ ታመስግናችኋለች” በሚል ሀሳብ ለሀገር የሰሩ የስነ ጥበብ ባለሙያዎች የምስጋና መርሃ ግብር በእንጦጦ ፓርክ አንፊ ትያትርና የስነ ጥበብ ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል።

የምስጋናና እውቅና ስነ ስርዓቱ በኪነጥበብ ለአገር አይረሴና የማይተካ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የትያትር ባለሙያዎች፣ ስዕልና ስነ ቅርፅ እንዲሁም የፊልም ጥበባት አንጋፋ ባለሙያዎች ናቸው።

በምስጋና መርሃ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የተገኙ ሲሆን አንቱታን ያተረፉ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ታዳሚ ሆነዋል።

(በአስታርቃቸው ወልዴ)

 

shares