ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሚደረጉ የእግር ኳስ ውድድሮችን ይመራል

ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ

ሚያዝያ 13/2013 (ዋልታ) – ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሚደረጉ የእግር ኳስ ውድድሮችን እንደሚመራ ተገለጸ፡፡

የተወሰኑ ወራት በቀሩት የቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ ተሳታፊ የሆነችው ኢትዮጵያ ከአትሌቲክሱ በተጨማሪ በእግር ኳስ ዳኝነት በኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ እንደምትወከል ነው የተገለጸው፡፡

ፊፋ በዛሬው እለት ባሳወቀው የዳኞች ዝርዝር በቶክዮ ኦሎምፒክ የሚደረጉ የእግር ኳስ ውድድሮችን እንዲመሩ ከመረጣቸው ዋና ዳኞች መካከል ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ አንዱ ሆኖ ተመርጧል።

“ሁሌም ስጠብቀው እና ሳልመው በነበረው የኦሎምፒክ ውድድር ላይ ሀገሬን በእግር ኳስ ዘርፍ በዳኝነት በመወከሌ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል” ሲሉ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ መናገራቸው ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችን

https://www.facebook.com/waltainfo
የአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/%D8%AA%D9%84%D9%81%D8%B2%D9%8A%D9%88%D9%86-%D9%88%D8%A7%D9%84%D8%AA%D8%A7-%D8%A8%D8%A7%D9%84%D8%B9%D8%B1%D8%A8%D9%8A-Walta-TV-Arabic-102134881551994/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የትዊተር ገፃችን
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!
shares