የመከላከያ ሚኒስቴር የ33ኛ ዙር ምልምል ወታደሮችን እያስመረቀ ነው

                             የ33ኛ ዙር ምልምል ወታደሮች

ሰኔ 22/2013 (ዋልታ) – የመከላከያ ሚኒስቴር የ33ኛ ዙር ምልምል ወታደሮችን በአሁኑ ሰዓት በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

በብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ሲሰለጥኑ የነበሩ ወታደሮች የተሰጣቸውን ስልጠና ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

ተመራቂዎቹ ከመደበኛው ሠራዊቱ ጋር በመቀላቀል ከውስጥና ከውጭ የሚቃጣን ወረራ በመመከት እንዲሁም የኢትዮጵያን አንድነት አጠናክው ያስቀጥላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የመከላከያ ሚኒስቴር የሰው ሃብት ልማት ዘርፍ ዋና ኃላፊ ሜጄር ጄኔራል ሐጫሉ ሸለመ፣ የምድር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ምክትል አዛዥ ለሰው ሀብት ልማት ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳንን ጨምሮ ከፍተኛ ጄኔራል መኮንኖች ተገኝተዋል።