የመራጮች ምዝገባ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

የመራጮች ምዝገባ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።
የምርጫ ቅድመ ዝግጅት ግምገማ ከክልል ፕሬዚደንቶች እና ከምርጫ ቦርድ ጋር መካሄዱን አስታውቀዋል።
የመራጮች ምዝገባ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እስካሁን ያልተመዘገባችሁ ዜጎች በተራዘመው የምዝገባ ጊዜ ተጠቅመው የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ አበረታታለሁ ብለዋል።
በምርጫ ጣቢያዎች የጸጥታ አካላት ምደባ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይ ሳምንታት እንደሚሰማሩ አስታውቀዋል።
የመጨረሻዎቹ የዴሞክራሲ ገንቢ እና ጠባቂዎች ራሳችን ኢትዮጵያውያን እንጂ ወዳጆቻችን አይደሉም ነው ያሉት።
ባለቤት ይወስናል፤ ወዳጅ ደግሞ ያግዛል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፤ የምርጫው ሂደት ስኬታማ እና ሰላማዊ እንዲሆን በጋራ እንሥራ ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልእክት አስተላልፈዋል።
shares