የረመዳን ፆምን በተሟላ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን በመተግበር እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ

ሚያዝያ 04/2013 (ዋልታ) – የረመዳን ጾም በሚከናወንበትና የስርዓተ እምነቱን የፆም ተግባራት በሚፈጽምበት ወቅት የኮሮና ወረርሽኝ መከላከያ መንገዶችን በመተግበር መሆን እንዳለበት የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡
ርቀትን መጠበቅ፣ የአፍና የአፍንጫ ማስክ መጠቀም እና እጅን በማጽዳት የግል መስገጃ ምንጣፎችን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ባለመጋራት መተግበር ያስፈልጋል ብሏል፡፡
እንዲሁም መላው ማህበረሰብ በእምነት ተቋማት ፣ በግብይት፣ በትራንስፖርት እና በሌሎች የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ሲገለገሉና ሲያገለግሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ማህበረሰቡ ራሱን እንዲጠብቅ ሚኒስቴሩ ጥሪ አስተላልፏል፡፡
ሚኒስቴሩ ለመላ ኢትዮጵያ ለሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1442 የረመዳን ጾም በሰላም አደረሳችሁ ማለቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
shares