የቦረናን እና የደቡብ ኦሞ ህዝቦችን የሚያገናኝ የጠጠር መንገድ  ተመረቀ

ሰኔ 04/2013 (ዋልታ) – የቦረናን እና የደቡብ ኦሞ ህዝቦችን የሚያገናኝ የተልተሌ-ዋዩ-ወንዶ-ኤርቦሬ የጠጠር መንገድ ግንባታ ተጠናቅቆ ተመረቀ፡፡

80.5 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የጠጠር መንገድ የኦሮሚያ ክልል መንግስት በበጀተው 1 ቢሊየን ብር ወጪ ነው ተብሏል፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የመንገዱ መገንባት ለክልሎች ግንኙነት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በመንገዱ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የሳይንስና ከፍተኛ ሚንስትር ሳሙዔል ኡርቃቶ፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ባውዲ እና ሌሎች የሁለቱ ክልሎች የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

(በሶሬቻ ቀበኔቻ)

shares