የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ውድድር ከእሁድ ጀምሮ በድሬዳዋ ይካሄዳል

የካቲት 16/2013 (ዋልታ)- 18ኛው የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ውድድር እና 14ኛው የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል ከየካቲት 21 እስከ 27 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ይካሄዳል፡፡

የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አስፋው ከትግራይ ክልል በስተቀር ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚሳተፉ ገልጸዋል፡፡

“የባህል ስፖርቶቻችን ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይህ ውድድር 11 የስፖርት ዓይነቶች ተካተውበታል፡፡

በውድድሩ 576 ወንዶች፣ 253 ሴቶች በጥቅሉ 829 ስፖርተኞች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡

ውድድሩ የሀገር ገፅታ የሚገነባበት እንዲሁም የተሰጡ ስልጠናዎች ውጤታማነታችው የሚለካበት እንደሆነ ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

shares