የኦሮሚያ የቀድሞ ፖሊስ አባላት ወደ ሥራ ሊመለሱ ነው 

ኅዳር 14/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ የቀድሞ ፖሊስ አባላትና የሥራ ኃላፊዎች አጭር ሥልጠና ከወሰዱ በኋላ የኦሮሚያን ፖሊስ ለመቀላቀል ዝግጁ መሆናቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ የቀድሞ አባላቱ ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቦ የነበር ሲሆን በቀረበው ጥሪ መሰረት ከበርካታ የኦሮሚያ ዞኖች ወደ ስራ ገበታቸው ለመመለስ ፍላጎት ያሳዩ አባላትና የሥራ ኃላፊዎችም በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ የአጭር ጊዜ ሥልጠና እየወሰዱ እንደሚገኙ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የቀድሞ አባላቱን ወደ ሥራ ገበታቸው ለመመለስ አስፈላጊው ዝግጅት ሁሉ መጠናቀቁንም ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አራርሳ መርዳሳ የቀድሞ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላትና የሥራ ኃላፊዎች አጭር ሥልጠና እየወሰዱ በሚገኙበት ተገኝተው እንዳበረታቷቸው ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡