ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሀረር ገቡ

መጋቢት 17/2013 (ዋልታ) – በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሚመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ሀረር ገባ፡፡
የልኡካን ቡድኑ ድሬዳዋ አየር ማረፊያ ሲደርስ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሃመድ ቡህ አቀባበል አድርገውለታል።
ልዑኩ በሚኖረው ቆይታ ሀረር የሚገኘው የፌስቱላ ሆስፒታል፣ ሸሪፍ ሙዝየምና ኢናይ አቢዳ የእደጥበብ ኮሌጅ እንደሚጎበኝ፣ የማገገሚያ ማዕከል እንደሚመርቁና የሰብዕና ምዕከል የመሰረት ድንጋይ እንደሚያስቀምጡ ከሃረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡