ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ከፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ ጋር ተወያዩ

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በኪጋሊ ከተካሄደው የአለም አቀፉ የስርአተ ጾታ ጉባኤ ጎን ለጎን ነው መሪዎቹ የተወያዩት፡፡

መሪዎቹ ሁለቱ ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነታቸውን ይበልጥ በሚያጠናክሩበት ሁኔታ ላይ የሀሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በሌላ በኩል ፕሬዝደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የተባበሩት መንግስታት የመጠለያ ጉዳዮች ድርጅት ሃላፊ የሆኑትን ማይሙና ሞድ አግኝተው አነጋግረዋል፡፡

ድርጅቱ በኢትዮጵያ እየሰራ ስላለው ስራ በዝርዝር ተነጋግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቷ በተጨማሪም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሶማሊያ ድጋፍ ሰጪ ቢሮ ሃላፊ የሆኑትን ሊዛ ፊሊፒቶን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

shares