ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 195 የህክምና ዶክተሮችን እያስመረቀ ነው

ሚያዚያ 02/ 2013 (ዋልታ) – የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንሰ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን 195 የህክምና ዶክተሮች እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርሲቲው እያስመረቃቸው ካሉት መካከል 38ቱ በተለያዩ የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራም የሰለጠኑ እንደሆኑ ተገልጿል።

ሁለት ተመራቂዎች ደግሞ ከኖርዌይ በርገር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በሶስተኛ ህክምና ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸውን የኮሌጁ ኤክስኪዩቲቨ ዳይሬክተር ዶክተር አንተነህ ጋደሳ ለኢዜአ ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲው ዶክተሮችን ዛሬ ሲያስመርቅ ለ12ኛ ጊዜ ሲሆን ስፔሻሊስቶችን ደግሞ ለ5ኛ ጊዜ መሆኑ ተወስቷል።