ሀገር አቀፍ የመስኖ ልማት ሥራዎች ከፍተኛ ለውጥ እያስገኙ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

የካቲት 28/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሀገር አቀፍ የመስኖ ልማት ሥራዎች ከፍተኛ ለውጥ እያስገኙ መሆናቸውን ገለጹ።

ለመጣው የመስኖ ልማት ስራው ለውጥ ማሳያው በዛሬው እለት የጎበኙት የአማራ ክልሏ ሜጫ  ወረዳ ናት ነው ያሉት።

በዚሁ ስፍራ 7 ሺህ 566 አርሶ አደሮች በ3 ሺህ 590 ሄክታር ላይ ባረፉ በ15 ኩታ ገጠም እርሻዎች ላይ፣ የቆጋን መስኖ በመጠቀም ስንዴን በውጤታማነት ማብቀል ችለዋል ብለዋል።

የመስኖ ልማቱ አነስተኛ የመሬት ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች  አቮካዶን በስኬታማነት እንዲያመርቱ እንዳስቻላቸውም ጠቅሰዋዕል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ክንውኑን ለመገምገም፣ ሞዴል አርሶ አደሮች እና የማኅበረሰብ መሪዎችን አግኝተዋል።

(ምንጭ፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)