ሁለንተናዊ ዝግጁነቱን ያረጋገጠ ሠራዊት ወሳኝ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሚያዝያ 29/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያን ከማንም፣ በምንም ሁኔታና መቼም ሉዓላዊነቷን ለማስከበር፤ ሁለንተናዊ ዝግጁነቱን ያረጋገጠ ሠራዊት ወሳኝ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁመራ በተካሄደው የምዕራብ ግንባር ሠራዊት የስልጠና ማጠቃለያ መድረክ በመገኘት ሰራዊቱን አበረታተዋል።

“ኢትዮጵያን ከማንም፣ በምንም ሁኔታና መቼም ሉዓላዊነቷን ለማስከበር፤ ሁለንተናዊ ዝግጁነቱን ያረጋገጠ ሠራዊት ወሳኝ ነው፡፡ በምዕራብ ግንባር ያየነውም ይሄንን ነው።” ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተመለከቱት የሠራዊቱ ዝግጁነት እጅግ አስደናቂ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡