ለተሰንበት ግደይ የ10,000 ሜትር ክብረወሰንን ሰበረች

ለተሰንበት ግደይ

ሰኔ 02/2013 (ዋልታ) – አትሌት ለተሰንበት ግደይ የ10,000 ሜትር የዓለም ክብረወሰንን ሰበረች፡፡

በኔዘርላንድ ሄንጌሎ በተደረገ ውድድር አዲስ የዓለም ክብረወሰን ያስመዘገበችው አትሌቷ፣ ከቀናት በፊት ለኔዘርላንድስ በምትሮጠው አትሌት ሲፋን ሀሰን ተሻሽሎ የነበረ ክብረወሰን ነው የሰበረችው።

በአትሌት አልማዝ አያና ለ5 ዓመታት ተይዞ የነበረውን የ10,000 ሜትር ክብረወሰን ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሀሰን ወስዳ መቆየት የቻለው ለሁለት ቀናት ብቻ ነው፡፡

አትሌት ለተሰንበት ግደይ ርቀቱን በ5 ሰከንድ በማሻሻል ክብረወሰኑን ወደ ኢትዮጵያ መልሳለች።

ለተሰንበት ውድድሩን 29:01:03 በሆነ ሰዓት በማሸነፍ ነው የክብረወሰኑ ባለቤት የሆነችው።

የሳምንታት እድሜ በቀረው የቶኪዮ ኦሎምፒክ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ከሲፋን ሀሰን ጋር የምታደርገው ውድድር ከወዲሁ በጉጉት የሚጠበቅ ሆኗል።