ለትምህርት ቤቶች “ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ” የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ ሆነ

ግንቦት 17/2013 (ዋልታ) – ለትምህርት ቤት አስተዳደር ሠራተኞች እና ለመምህራን የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን መከላከል እና ለቁጥጥር ሥራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለመስጠት “ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ” መተግበሪያ ይፋ ሆነ።
የግንዛቤ ማስጨበጫ መተግበሪያው ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ርእሰ ጉዳዮችን ማካተቱ ተገልጿል።
የኮሮና ቫይረስ መተግበሪያው በጤና እና ትምህርት ሚኒስቴር በጋራ የተዘጋጀውን የኮሮና ቫይረስ መከላከል መመሪያን መሠረት ያደረገ ነውም ተብሏል፡፡
መተግበሪያው የበሽታ ቅኝት፣ የተግባቦት እና የማኅበረሰብ ተሳትፎ ሥራዎችን እንዲሁም በሁሉም ደረጃ ስላለው ኃላፊነቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
በመጨረሻም “ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ” መተግበሪያን ሁሉም መምህራን እና የትምህርት ቤት አስተዳደር ሠራተኞች በስልካቸው በመጫን ስልጠናውን እንዲወስዱ እና ለኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ቁጥጥር ሥራ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ ማቅረቡን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡