ለ15 ዓመታት የሚቆይ የጤና ኤክስቴሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ

የካቲት 24/2013 (ዋልታ) – በጤና ሚኒስቴር አስተባባሪነት ለ15 ዓመታት የሚቆይ የጤና ኤክስቴሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ይፋ መሆኑ ተገለፀ።

“የጤና ኤክስቴንሽ ፕሮግራምን በማሻሻል ሁለንተናዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ማረጋገጥ” በሚል መሪ ሐሳባ ይፋ የሆነው የጤና ኤክስቴክሽን ፕሮግራም ከ2013 እስከ 2027 የሚቆይ እንደሆነም ተጠቁሟል።

ማሻሻያ ፕሮግራሙ ፍኖተ ካርታ ማድረጊያ መርሃ ግብር ላይ ምክትል ጠቅላይ ምኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮነን እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰን ጨምር ጥሪ የተደረገላቸው ሚኒስትሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

(በምንይሉ ደስይበለው)