ሊዲያ ታፈሰ የወንዶችን የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ትመራለች

ኢትዮጵያዊቷ ሊዲያ ታፈሰ የቻን የአፍሪካ ዋንጫ በዋና ዳኝነት የምትመራ ብቸኛዋ ሴት መሆኗን የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

በካሜሮን አዘጋጅነት የሚካሄደው የቻን የአፍሪካ ዋንጫ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ኮሚቴ ከ31 ሀገራት 47 ዋና ዳኞች ፣ ረዳት ዳኞች እና የቪዲዮ ረዳት ዳኞችን መርጧል።

በተመሳሳይ ሌላኛው ዓለም አቀፍ ዳኛ በአምላክ ተሰማ በቫር ዳኝነት የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ከሚመሩ ዳኞች መካከል አንዱ ሆኖ ተመርጧል።

የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ከጥር 8 ቀን 2013 እስከ ጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በካሜሮን አዘጋጅነት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።