ማሊ ከአፍሪካ ህብረት አባልነት ታገደች

አፍሪካ ህብረት

ግንቦት 25/2013 (ዋልታ) – በቅርቡ በማሊ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት ማሊን ከህብረቱ አባልነት ማገዱን ይፋ አደረገ፡፡

ማሊ ከህብረቱ አባልነት የታገደችው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ በአገሪቱ ለ2ኛ ጊዜ በመፈንቅለ መንግስት መደረጉን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

ማሊ በአፋጣኝ በአገሪቱ ሕገ መንግስታዊ ስርዓት እንዲሰፍን እንድታደርግና በሲቪል የሚመራ መንግስት እንድታቋቁም ህብረቱ ጠይቋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት በመፈንቅለ መንግስት የሀገሪቱን በትረ ስልጣን የያዘው ወታደራዊ ሀይል  ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወታደሮቹን ወደ ካምፕ እንዲመልስ የጠየቀ ሲሆን፣ ይህንን ተግባራዊ ካላደረገ ግን በማሊ ላይ ማእቀብ እንደሚጥል ማስጠንቀቁን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡