ሩዋንዳ ለጤና ባለሙያዎች የኮሮናቫይረስ ክትባት መስጠት ጀመረች

                             በሩዋንዳ የኮሮናቫይረስ ክትባት

ሩዋንዳ ለጤና ባለሙያዎች የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት መስጠት መጀመሯን የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴሩ ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ በፋይዘር የተመረተው የኮሮናቫይረስ ክትባት በዋና ከተማዋ ኪጋሊ ውስጥ በሚገኙ የተወሰኑ ሆስፒታሎች ይሰጣል።

ክትባቶቹ በተወሰነ መጠን በዓለም አቀፍ እርዳታ እንደተገኙ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ክትባት መስጠት ከጀመሩ የአፍሪካ አገሮች መካከላ ግብጽ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ሞሪሽየስ እና ሲሸልስ ይገኙበታል።

የሩዋንዳ የጤና ሚኒስቴር እንዳለው በርካታ ቁጥር ያለው ጠብታ በዚህ ወር ይሰጣል። ይህም በአፍሪካ ሕብረት በኩል በኮቫክስ ጥምረት የሚገኝ ክትባት ነው።

ሩዋንዳ ውስጥ እስካሁን 17,000 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 239 ሞተዋል። አገሪቷ 200,000 ጠብታ እንዳገኘችም ተጠቁሟል።