ራይዚንግ ኢትዮጵያ በሚል ሃሽታግ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጀመረ

ራይዚንግ ኢትዮጵያ በሚል ሃሽታግ የተሳሳቱ የመገናኛ ብዙኀን ትርክቶች ለማረቅና የኢትዮጵያን መልካም ጎን ለማስታዋወቅ ያለመ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ኢትዮጵያ እና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ትብብር የተዘጋጀው ዘመቻ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎችን እንደሚያስተባብር ተገልጿል፡፡

በዘመቻው ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት እምቅ አቅም፣ ባህል፣ የቱሪስት መዳረሻዎችን፣ በጎ አድራጎትን እና ፕሮጀክቶችን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ያስተዋውቃልም ተብሏል፡፡